• – ድርጅቱ መደበኛ፣ የክብርና ተባባሪ እየተባሉ የሚጠሩ አባላት ይኖሩታል፡፡
 • – የአባልነት መብት ለወራሾችም ሆነ ለሌላ ሰው የማይተላለፍ የግል መብት ነው፡፡

የማህበሩ መደበኛ አባል የሚሆነው፡-

 • – የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሃይማኖት ተከታይና የሰበካ ጉባዔ አባል የሆነ፣
 • – የድርጅቱን ዓላማ የተቀበለ፣
 • – በጠቅላላ ጉባዔው የተወሰነውን ወርሀዊና ዓመታዊ የአባልነት መዋጮ ለመክፈል    የተስማማ፣
 • – ማህበሩን በሙያ፣ በጉልበትም ሆነ በገንዘብ ለመርዳት ፈቃደኛ የሆነ፣
 • – ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ፣
 • – ከዚህ በላይ የተመለከቱትን መስፈርቶች አሟልቶ የማህበሩ አባል ለመሆን ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ያገኘ ሰው የማሕበሩ አባል ነዉ፡፡

ልዩ ልዩ ሁኔታዎች፣

ልዩ ልዩ ሁኔታዎች፣

ከተጋቢ ወገኖች ውስጥ አንዱ የድርጅቱ አባል እንዲሆን አመልክቶ ከተፈቀደለት ሁለቱም ባልና ሚስት የማህበሩ አባል ይሆናሉ፡፡ ሆኖም ተጋቢ ወገኖች ድርጅቱ አባል ከሆኑ በኋላ ጋብቻቸው ከፈረሰ እያንዳንዳቸው ወርሀዊ ክፍያቸውን በየግላቸው በመክፈል በአባልነት ሊቀጥሉ ይችላሉ፡፡

የክብር አባልና ተባበሪ አባል፣ የክብር አባል፣

 • – የድርጅቱ መደበኛ አባል የሆነና ለድርጅቱ ከፍተኛ አገልግሎት ያበረከተ የክብር አባል ሆኖ መመረጥ ይችላል፡፡
 • – ለማህበሩ ዓላማ መሳካት የላቀ አስተዋጽኦ ያደረጉ ታዋቂ አባላት በሥራ አመራር ቦርድ አቅራቢነት ጠቅላላው ጉባዔው የክብር አባል አድርጎ ሊሰይማቸው ይችላል፡፡

ለክብር አባልነት የሚያበቁ መመዘኛዎች፣

በአባልነት ከ10 ዓመት ያላነሰ የቆየና ያገለገለ፣

 1. በአመራር አባልነት ተመርጦ ጊዜውን ያለምንም ችግርና እንቅፋት የፈጸመ፤
 2. በተለያዩ ኮሚቴዎች ውስጥ ተመርጦ የሰራና አመርቂ ውጤት ያስመዘገበ፤
 3. ለድርጅቱ በጉልበት፣ በሞራል፣ በገንዘብና ቁሳቁስ፣ አስተዋጽዖ ያደረገ፤
 4. አለመግባባቶች ሲከሰቱ ለመፍታት ጉልህ አስተዋፅኦ ያደርገና ለድርጅቱ ህልውና የቆመ፤

ተባባሪ አባል፣

 • የድርጅቱን ዓላማ በመደገፍ ድርጅቱን በገንዘብና በቁሳቁስ የሚረዳ ማናቸውም ሰው የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ካመነበት በተባባሪ አባልነት ሊቀበለው ይችላል፡፡
 • –   ተባባሪ አባል የመምረጥና የመምረጥ መብት የለውም፤ድምፅ አይሰጥም፡፡
 • ግዴታቸውን የተወጡ የድርጅቱ መደበኛና የክብር አባላት እንደ አባልነታቸው ተመዝግበው መታወቂያ ይሰጣቸዋል፡፡

የአባላት መብት

 • በድርጅቱ አመራር አባልነት መመረጥና መምረጥ፤
 • በድርጅቱ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን፤
 • በድርጅቱ ስብሰባ መካፈል፣ ሀሳብን ማቅረብ፣ አስተያየት መስጠት፣ ቅሬታ ማሰማትና በሚተላለፉ ውሳኔዎች ድምጽ መስጠት፤
 • ድርጅቱ በሚያዘጋጀው በማናቸውም ጉዞ፤ ስለጉዞው የተደነገገውን መስፈርት በሟሟላት መመዝገብና በጉዞ መካፈል፣
 • አባሉ በራሱ ፈቃድና ምክንያት ከአባልነት ሊሰናበት ይችላል፡፡
 • አንድ አባል ከአባልነት ከተሰናበተ በኋላ እንደገና የድርጅቱ አባል ለመሆን በጽሁፍ ሲጠይቅ በስራ አመራር ቦርድ ተቀባይነት ካገኘ በኋላ ለጠቅላላ ጉባዔ ቀርቦ በሚሰጠው ውሳኔ መሰረት እንደገና የድርጅቱ አባል ይሆናል፡፡
 • ስለ ማሕበሩ እንቅስቃሴ መረጃ የማግኘት፤
 • ማንኛውም አባል ከድርጅቱ ሲወጣ ጥቅማጥቅም የመጠየቅ መብት የለውም፡፡

የአባላት ግዴታዎች

 • ጠቅላላ ጉባዔ ወይም የሥራ አመራር ቦርድ በውስጠ ደንቡ የወሰነውን ወርሃዊ ክፍያና አንደ ሁኔታው የተጣለበትን መዋጮ አጠናቆ መክፈል፣
 • በመደበኛ አባልነት ለመግባት ጠይቆ የተፈቀደለት አባል በቅድሚያ የመመዝገቢያ ክፍያ መክፈል፣
 • የድርጅቱን መመሪያ፣ ውሳኔና ትዕዛዝ ማክበርና ተግባራዊ ማድረግ፣
 • የድርጅቱን ዓላማዎች ከግብ ለማድረስና ድርጅቱን ለማጠናከር ለሚደረገው ጥረት በማናቸውም የድርጅቱ ተግባራት ውስጥ ተሳታፊ መሆን፣
 • የድርጅቱን የስብሰባ ጥሪ አክብሮ መገኘት፣
 • የድርጅቱን ክብር መልካም ስምና ዝና መጠበቅ፣
 • ድርጅቱን ለማጠናከርም ሆነ ለአስፈላጊ ተግባራት በኮሚቴ አባልነትና በመሳሰሉ መካፈል፡፡
 • ድርጅቱን ሀብትና ንብረት እንዲጠበቅ የበኩሉን ክትትል ማድረግ ጉዳት መድረሱን ሲያዉቅ ማሳወቅ፡፡
 • የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነት መከታተል ዉጤቱን ኃለፊነቱን ለሰጠዉ አካል   በወቅቱ ማቅረብ፡፡
 • ከጠቅላላ ጉበዔና በሥራ አመራር ቦርድ የሚሰጡትን ተግባራት ማከናወን፡፡

አባልነት የሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች

 • ድርጅቱን የሚጎዳ ተግባር የፈጸመ እንደሆነ ወይም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖቱን የለወጠ መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ፣
 • ለአባላት በሚሰራጨው አጀንዳ ላይ በተገለጸ ስብሰባና ጥሪ በተደረገበት ሌላ ስብሰባ ከአቅም በላይ ካልሆነ በስተቀር አንድ ዓመት በተከታታይ ያልተገኘ፣
 • በጉዞም ሆነ በሌላ ጊዜ የድርጅቱን ስም የሚያጎድፍ ተግባር የፈጸመ ወይም በምርጫ ሂደት፣በሰብሳቢዎች ሆነ ብሎ ሁከት በመፍጠር ስብሰባዎችን በተደጋጋሚ ያደናቀፈ፤
 • የድርጅቱን ንብረትና ገንዘብ ያለአግባብ ያጠፉ ወይም በሌላ ሰው እንዲጠፋ ሲያደርግ ወይም ያደረገ፡፡
 • በራሱ ፍላጎት ከድርጅቱ ለመሰናበት በፅሁፍ ሲጠይቅ፡፡
 • በሞት ሲለይ፡፡
 • በጠቅላላ ጉበዔ ወይም በቦርዱ ተመርጦ የተሰጠዉን ኃላፊነት ሳይወጣ ቀርቶ ጉዳት ሲያደርሰ፣
 • በማንኛዉም አመራር ዉሰጥ ተመርጦ የምርጫ ጊዜ ሲያበቃ በጉባዔ እንዲራዘም ሳይወሰን በራሱ ዉሣኔ ቀጥሎ ከተገኘ፡፡
 • በተመራጭነቱ ኃላፊነቱን ከመጠኑ በማለፍ ከድርጀቱ ያልተያዘ በጀት ገንዘብ ወይንም ንብረት እንዲወጣ ያደረገ በበጀት የተያዘዉንም ያለአግባብ ያባከነ፡፡

የጉዞ ፕሮግራም አተገባበር፣

 • ወደ ኢየሩሳሌም ሆነ ሌላ ቦታ ለሚደረግ ጉዞ አባላት የሚመዘገቡበትን የጊዜ ሰሌዳ ቦርዱ ሲወስን፤ ጽ/ቤቱ በሥራ አስኪያጁ አመራር ሰጭነት ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
 • በጉዞው ወቅት ለአባላት፤ ለጉብኝትና ለፀሎት አመቺ በሆነ አካባቢ ማረፊያና ማጓጓዣ እንዲዘጋጅ መደረጉን ቦርዱ ይከታተላል ያረጋግጣል፡፡ በተለይም ተጓዡ የተጓዘበትን በበቂ ተረድቶ እንዲመለስ ጥልቅ እውቀትና በቂ ችሎታ ያላቸውን አስረጂዎች ያዘጋጃል፡፡
 • በጉዞ ወቅት የድርጅቱን ህልውናና ለወደፊቱም የጉዞ ዓላማ ለማሳካት እንዲቻል ቦርዱ ተጓዦቹን በጥልቀት አውቆ መለየት ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፡፡
 • ለጉዞ አመቺ የሆነ መመሪያ በማውጣት ተግባራዊ ያደርጋል፤ ስለ ጉዞ አፈጻጸም የዚህን ውስጠ ደንብ ተፈጻሚ ያደርጋል፡፡ ተጓዥ አባላት የሚገበኙበትን ሥፍራ ጥልቅ ግንዛቤ እንዲኖራቸው፤ ብሮሸሮች አዘጋጅቶ ያድላል፡፡ በወርሃዊ ስብሰባዎችም ላይ በቂ ትምህርት ይሰጣል፡
 • ከጉዞ መልስ አጠር ያለ ሪፖርት በማዘጋጀት የክብር አባላት ታዋቂና ነባር አባላት ባሉበት በሪፖርቱ ላይ መወያየትና ደካማና ጠንካራ አሰራሮችን በመለየት ለወደፊቱ አሰራር የሚበጅ አቅጣጫ የሚያስይዝ ለጠቅላላ ጉባኤ የውሳኔ ኃሳብ ያቀርባል፣

በኢየሩሳሌም ገዳማትን ለማስከበር፡-

 • የተወሰዱ ገዳማትና ንብረትን ለማስመለስ በሚደረገው ጥረት ላይ ከመሳተፍ ባሻገር የንብረትነቱ ሁኔታ ከእጅ የወጣበትን ምክንያት በማጥናትና በመለየት፤ የተወሰደው ንብረት እንዲመለስ አባላትን በማስተባበር እንደአስፈላጊነቱ ለሚመለከተው ሁሉ በማቅረብ የበኩሉን ጥረት ያረጋል፡፡
 • የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በኢየሩሳሌም የሚገኙትን ገዳማትና ታሪካዊ ቦታዎች ፈራርሰው ከመጥፋታቸው በፊት እድሳት ተደርጎ ታሪካዊነታቸው እንዲጠበቅ ከሚመለከታቸው ጋር ሁሉ ትብብር ያደረጋል፡፡
 • –  ድርጅቱ በኢየሩሳሌም ለአባላት ማረፊያ ለማዘጋጀት ዓላማ አድርጎ በዕቅድ በመያዝና ወደ ተግባር ለመለወጥ የተቻለውን ሁሉ ያረጋል፡፡

ጥያቄ አሎት?

Your Name

Your Email

Your question