ስለ ኢትዮጵያ የታሪክ ይዞታ ጥበቃ በሠላሳዎቹ ተሳላሚዎች የተደረገ ውይይት

የአንድ አገር ሕዝብ ትልቅነቱ የሚለካው በታሪኩ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በአገር ውስጥና በባሕር ማዶ በኢየሩሳሌም ባሉዋት የቅድመ ታሪክ ይዞታዎዋ አምራና አሸብርቃ ኖራለች፡፡ ወደፊትም ትኖራለች፡፡ በተለይም ከአፍሪካ ክፍለ ዓለም ማለትም ከጥቁር ዓለም በኢየሩሳሌም ውስጥ በቅድመ ታሪክ አብባና አፍርታ የምትታየው አፍሪቃን ወክላ ነው፡፡ ውክልናዋ የታሪክ ምስክር ሆኖ እያለ በአገር ርቀትና በመገናኛ እጦት እንዲሁም በአካባቢዋ በተፈጠረ ችግር ኢትዮጵያውያን በእግራቸው ለመርገጥ፣ ይልቁንም እኛ አባቶቻችን ናቸው የምንላቸው ደማችንን እየጠጡ፣ አጥንታችንን እየቆረጠሙ የኖሩት ግብጻውያን የኢትዮጵያን የታሪክ ይዞታ በግፍ ቀምተዋል፡፡ ለሌሎችም አሳልፈው ሸጠዋል፡፡ ቤተ መቅደሳችንን በመዝጋት መብራትና ውሀ ወደ ታሪካዊ ይዞታችን እንዳይገባ አድርገዋል፡፡ በመንፈሳዊ አገልግሎት የሚኖሩ ወገኖቻችንን ከአደረሱባቸው የኑሮ ስቃይ የተነሣ ቦታውን ለቀው እንዲሄዱ በማድረግ የዋሉባቸውን ግፍ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሊረሳው አይገባም፡፡

በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ግፍ መርምሮ የተገነዘበ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ፍርዱን ሊሰጥ ይችላል፡፡ ብለዋል፡፡ በጆሮዋቸው የሰሙትን በዓይናቸው የአዩዋቸውን በልቡናቸው የአገናዘቡ የÚ»êÞ° ዓ.ም ተሳላሚዎች ምን እናድርግ ብለው ሲጨነቁ የእግዚአብሔር ፍቃዱ ሲሆን ሥራውንና ቸርነቱን የሚገልጸው በሰው እያደረ እንደመሆኑ አቶ መኰንን ዘውዴን መሣሪ አድርጎ በማየታቸው የወገንና የታሪክ ይዞታ ጥቃት እንደ ተሰማቸው “ድርጅት አቋቁመን” ለወገኖቻችን ለኢትዮጵያውያን ቅዱሳን መካናትን ለመሳለም የሚያበቃ መንገድ ብንከፍት በየዓመቱ በመቶ የሚቆሩ ኢትዮጵያውያን በኢየሩሳሌም አደባባይ እየተገኙ ቦታቸውን ያስከብራሉ፡፡ ለወገኖቻችንም የመንፈስ ጥንካሬ ይሰጣሉ የተዘጉ አብያተ መቅደሶቻችን አስከፍተን በቁጥጥራችን ሥር እናደርጋለን፡፡ መብራትና ውሀ ያጣ ገዳማችንና ያለኤሌክትሪክ መብራት የሚኖሩ ወገኖቻችንን ከችግራቸው ሁሉ ለማዳን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ቆሞ እኛም ምክንያት እንሆን ይሆናል፡፡ ብለው በጊዜው አብረዋቸው ለተጓዙት ተሳላሚዎች የመልካም ምኞት ኃሳባቸውን ገለጡላቸው፡፡

ሁሉም ተጓዦች “አንተ ካስተባበርከን እኛም የበኩላችን በምንጠይቀው ሁሉ እንሰለፋለን” በማለት በድጋሚ የማበረታቻ መልስ ሰጥተዋቸዋል፡፡

ተሳላሚዎቹ የጉብኝት ጊዜያቸውን ፈጽመው ወደ አገራቸው በመመለስ ላይ ሳሉ ለገዳማቱ መረጃ ገንዘብ ለማዋጣት ተወያዩ፡፡ ሆኖም በዚያን ጊዜ ለመጓጓዢያ ወጭ ያደረጉት ገንዘብ በዛ ያለ በመሆኑና ምንም እንኳን በቂ ገንዘብ ባይዙም ከዚያው ካላቸው ቀንሰው ሊሰጡ ስለ ፈለጉ የገንዘብ ማዋጣቱን ሁኔታ ገፍተውበታል፡፡ ከተሳላሚዎቹ አንዱ ክቡር አቶ መኰንን ዘውዴ የብዙዎቹን አስተያያት ከአዳመጡ በኃላ አሁን አዋጥተን ከመነኮሳቱ የምንሰጣቸው ገንዘብ አይጠቅማቸውም፡፡

የወገኖቻችን መጠቃትና ችግር በዓይናችን በማየታችን የጥቃቱ ትዝታ ከአእምሮአችን ሳይጠፋ ወደ አገራችን እንደ ተመለስን ኢትዮጵያውያን ይህንን ለመሰለ ጉዳይ ቀጥተኞች ስለሆኑ ጠንካራ ማኀበር አቋቁመን ኢትዮጵያውያን በብዛት ወደ ዚህ ቅዱስ ቦታ እንዲመጡ ማድረግ አለብን በማለት ሐሳብ አቅርበውላቸዋል፡፡

ሃያ ዘጠኙ ተሳላሚዎች ክቡር አቶ መኰንን ዘውዴን “ አንተ ሰብስበህ ካስተባበርከን እኛ በደስታ እንከተልሃለን” ብለው በድጋሜ ቃል ገብተውላቸዋል፡፡ ሆኖም ተሳላሚዎቹ በሙሉ ክቡር አቶ መኰንን ዘውዴ ጭምር እያንዳንዳቸው የተቻላቸውን ጊዜያዊ እርዳታ ለገዳሙ ለግሠው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል፡፡ አገራቸው ኢትዮጵያም እንደ ደረሱ በወራት ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንን የሚያሰባስብ ግዙፍ ድርጅት እንዴት ማቋቋም እንደሚችል ጥልቀትና ስፋት ያለው ጥናት አካሄዱ፡፡

ከጥቂት ወራት ቆይታ በኃላ የሠላሳዎቹን ተሳላሚዎች የጉዞ ሁኔታ፣ የጎበኙዋቸውን ቅዱሳን መካናትና ታሪካዊ ስፍራዎችን ቅድስና አስመልክተው ክቡር አቶ መኰንን ዘውዴ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ መግለጫ ሰጡ፡፡

በዚህ መሰረት ብዙዎች ኢትዮጵያውያን የድርጅቱን መቋቋም በሙሉ ልብ ስለ ደገፉትና በሥራም ስለተባበሩ የካቲት Ú¤ ቀን Ú»êÞ¤ ዓ.ም “ የኢትዮጵያ ምእመናን መታሰቢያ ድርጅት ለኢየሩሳሌም” በሚል ስያሜ ይህ ታላቅ ድርጅት በኮሚቴ አባላቱ ተቋቋመ፡፡

ከዚህ በኃላ ለብርቱ ሰው ሥራ ኃይልና ብርታት የሚሰጡት ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ መልካም ፈቃዳቸው ሆኖ የድርጅቱን መቋቋም እንዲፈቅዱና በግርማዊነታቸው ተደግፎ የቆመ ድርጅት እንዲሆን አንድ ማስታወሻ ለግርማዊነታቸው ለማቅረብ ኮሚቴው ወሰነ፡፡

በውሳኔው መሰረት የቀረበ ማስታወሻ

ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት

ግርማዊ ሆይ

በኢየሩሳሌም ቅዱሳት መካናትን ለመሳለም ስንሄድ ከግርዊነትዎ ዙፋን ቀርቤ ስሰናበት ስለዴር ሡልጣን የተደረገውን ድካም በማስታወስ ኢትዮጵያውያን በብዝት እየሄዱ እንዲሳለሙና በኢትዮጵያ ገደም የበዓሉ ተካፋይ እንዲሆን ከግርማዊነትዎ መልካም ፈቃድ መሆኑን ማወቅ ችያለሁ፡፡

ማየትና መስማት የተራራቁ ስለሆነ ግብፆች በዴር ሡልጣን ያደረጉትን የሚያደርጉትን ጭቆ በሥፍራው ተገኝቶ ሲታይ ጥቃቱ በይበልጥ ይሰማል፡፡

ቢሆንም እግዚአብሔር ለግርማዊነትዎ የማያልቅበትን ረዥም ዕድሜ ከፍፁም ጤንነት ጋር ይስጥልን እንጂ የጀመርነውን ከግቡ ማድረስ ለግርማዊነትዎ የተለየ ዕድል ስለሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጉዳዩ ፍፃሜ እንደሚያገኝ ይታመናል፡፡

ኢትዮጵያውያን ምእመናን ወደ ኢየሩሳሌም እየሄዱ በኢትዮጵያ ገዳም በሚደረገው ሥነ በዓል ተካፋይ ቢሆኑ ግርማዊነትዎ ለሚደክምበት ለዴር ሡልጣን የኢትዮጵያ ገዳም በዳኝነት ለሚመለከቱት አሳሳቢ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ይህንም ያልኩበት በዚህ ዓመት መነኮሳትና ሠራተኞ ጋር በቁጥጥራቸው ወደ መቶ ስለተቃረበ ከወዴት መጡ እያሉ ግብጾች መጠየቃቸውን ክቡር አቶ ሣላህ ሂኒትና የገዳሙ ጠበቃ ሰምተው ለብፁዕ አባታችን አቡነ ፊልጶስ ነግረዋቸው ብፁዕነታቸው ገልጸውልናል፡፡

በየዓመቱ ወደ ኢየሩሳሌም መሔድ ጠቃሚ መሆኑ ቢታመንም ብዙ ኢትዮጵያውያን ሲሔዱ ማረፊያ ማዘጋጀት ተቀዳሚ ሥራ ሆኖ ይታያል፡፡

በዚህ ዓመት የሔዱት ኢትዮጵያውያን አንድ ድርጅት አቋቁመን ለሕዝቡ እናስረዳ የማለት አሳብ አድሮባቸው በኔ አስታዋሽነት እንድንነጋገር በጥብቅ አስገንዝበውኛል፡፡

“በኢየሩሳሌም ቅዱሳት መካናት ጎበኘን” በሚል አርእስት በራዲዩን ያሰማሁትንና በጋዜጣ የታተመውን መነሻ በማድረግ ብዙ ሰዎች በሚመጣው ዓመት ወደ ኢየሩሳሌም ለመሔድ የጋለ ምኞት ሲኖራቸው እንዲያውም በየዓመቱ ወደ ኢየሩሳሌም በሚሔዱ ምእመናን ስም ድርጅት ቢቋቋም የሚል ድምፅ ያሰማል፡፡  

ይሁን እንጂ በኢየሩሳሌም ያሉ የኢትዮጵያ ገዳማትን በአስተዋጽኦ ለመርዳት ካሁን በፊት ማኀበር ተቋቁመዋል፡፡ ግርማዊነትዎ የማኀበሩ የበላይ ጠባቂ ሲሆን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ የኢትዮጵያ ፓትርያርክ የክቡር ፕሬዝዳንት መሆናቸውን ሰኔ Ú» ቀን Ú»êÝ° ዓ.ም በታተመው የማኀበሩ መተዳደሪያ ደንብ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ስለ ኢየሩሳሌም ገዳማት የተቋቋመ ማኀበር እያለ አሁን የታሰበውን ድርጅት ለማቋቋም ከመሞከር በፊት ጉዳዩን ለግርማዊነትዎ ማመልከት ወደድሁ፡፡ ካሁን ቀደም የተቋቋመው በኢየሩሳሌም ያሉ የኢትዮጵያን ገዳማት በአስተዋፅኦ ለመረዳት ሲሆን አሁን የታሰበውን “በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያውያብ ምእመናን መታሰቢያ ድርጅት” በሚል ስም ለማቋቋም ነው፡፡ ይህን ድርጅት አቋቁሞ ሥራውን ለመከተል በግርማዊነትዎ መልካም ፈቃድና አስተያየት መደገፍ የመጀመሪያ የሥራው ዓላማ ስለሆነ ወደሥራው ጠልቆ ለመግባት የግርማዊነትዎን ፈቃድ በታላቅ ትህትና እለምናለሁ፡፡

የግርማዊነትዎ ፍጹም አገልጋይ

መኰንን ዘውዴ

የድርጅቱ መቋቋም በግርማዊነታቸው ተደግፎ እንደተፈቀደ ድርጅቱን በዋና ሥራ አስኪጅነት የሚመሩት አቶ መኰንን ዘውዴ ጊዜያዊ ደንብ ካዘጋጁ በኃላ በቅድስት አገር ጉዞ ወቅት ቃል ኪዳን ከገቡት ጥቂቶቹንና የድርጅቱን የማቋቋም ሓሳብ በመደገፍ የተባበሩዋቸውን ለሌሎች የሙያ ሰዎች ሰብስበው በደንብ ረቂቅ ላይ ከተወያዩ በኃላ የደንቡን ጽሑፍ አዘጋጅተው ጉዳዩ ለሚመለከተው መሥሪያ ቤት ማለትም በዚያን ጊዜ የአገር ግዛት እየተባለ ለሚጠራው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት አቅርበው የድርጅቱን ሕጋዊ አቅዋም በሕግ አስፈቀዱ፡፡