ድርጅቱ ከመነሻው የተቋቋመበት ምክንያት፣

ድርጅቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ፣

ornament1

  • በኢየሩሳሌም ለሚገኙ ገዳማትና መነኮሳት በየዓመቱ ስንቅ በማቅረብ፣ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ በመስጠት፣
  • በኢየሩሳሌም ደብረገነት ኪዳነምህረት ገዳማችን ግቢ ውስጥ ትልቅ ሠፊ አዳራሽና ማረፊያ ቤቶችን ሠርቶ ለምዕመናንና ለጳጳሳት ማረፊያ በበዓላት ወቅት መሰብሰቢና መመገቢያ ሆኖ እንዲያገለግል በማድረግ፣
  • በየዓመቱ ለትንሣኤ በዓል በኢየሩሳሌም ለሚገኙ መነኮሳት ለፆም መፈሰኪያ የሚውሉ ምግቦችንና ቁሳቁሶችን ከአዲስ አበባ እያጓጓዘ በማቅረብ፣ ይህንንም ተግባሩ ላለፉት 54 ዓመታት በተከታታይነት ሲያከናውን መቆየቱ፡፡

በሀገር ያደረጋቸውን አስተዋጽኦ ፣

ornament1

  • የአዲስ አበባ መስተዳድር የጎዳና ተዳዳሪ ታዳጊዎችን ለማቋቋም ለጀመረው ተግባር  የግማሽ ሚሊዮን ብር ድጋፍ በማድረግ፡፡
  • የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ በከፍተኛ ደረጃ እየተረባረቡበት ለሚገኘው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የግማሽ ሚሊዮን ብር ቦንድ በመግዛትና ጊዜው ሲያልቅም እንደገና በድጋሚ በዚሁ መጠን በመግዛት፣
  • በጦርነት ምክንያት ወላጆቻቸውን ያጡ ቁጥራቸው ከአንድ ሺህ በላይ የሆኑ ሕጻናትን ተንከባክቦ በማሳደግና በማስተማር፣

ሌሎች ያስገኛቸው ጥቅሞችን ፣

ornament1

  • ድርጅታችን በየዓመቱ ከ300 የማያንሱ ምዕመናን ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም እየሄዱ  ጎብኝተው መንፈሳዊ ተግባራቸውን ፈጽመው እንዲመለሱ እያደረገ መሆኑ፣
  • የኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የሚገኙ ገዳማትንና መነኮሳትን ማገዝ ብቻ ሳይሆን የሀገራችን ንብረት የሆኑ ቅርሶችን በመጠበቅና በመንከባከብ ለሀገራችንና ለኅበረተሰቡ ተጨባጭና ጉልህ አስተዋጽኦ እየሰጠ የሚገኝ መሆኑ፣

የድርጅቱ የበላይ ጠባቂ

ornament1

– የድርጅቱ የበላይ ጠባቂ፤በጠቅላላ ጉበዔዉ የተመረጡት አባላት  ሲቀርቡ አባታዊ ምክርን       ይሰጣሉ፡፡በድርጀቱ ዉሰጥ ሰላምና ፍቅር የሚሰፍንበትን ሃይማኖታዊ ትምህርተ ይሰጣሉ፡፡በማህበሩ አባላት ሃይማኖት ነክ የሆነ አለመግባባት ሲፈጠር መፍትሔ ይሰጣሉ፣- ወደ ቅደሰት ሀገር ኢየሩሳሌም ጉዞ በሚደረግበት ወቅት ከቅዱሰ ሲኖደስ አባላት ዉሰጥ ትምህርት፣ ምክርና ቡራኬ እየሰጡ የሚጓዙ አባት ይመድባሉ፡፡

1

በ1955 ዓ.ም ለመንፈሳዊ ጉብኝት ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው የነበሩ ሠላሳ ያህል ኢትዮጵያውያን በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የኢትዮጵያ ገዳም ሲጎበኙ በወቅቱ በስፍራው የነበሩት መነኮሳት ስንቃቸው አልቆ በቅርብ ተገኝቶ የሚረዳቸው አለመኖሩን፣ በየጊዜው በግብፆች በሚደርስባቸው በደልና ጉዳት ሳቢያ ከፍተኛ ችግር ደርሶባቸው በተጎሳቆለ ሁኔታ መኖራቸውን ስለተመለከቱ መነኮሳቱም ወገኖቻቸውን ሲያገኙ አልቅሰው ችግሮቻቸውን በመናገር በየጊዜው ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ጨምረው ተመልሰው እንዲመጡ ቃል አስገብተው ስላሰናበቷቸው ወደ ሀገር ቤት እንደተመለሱ በገቡት ቃል መሠረት የኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅትን መሠረቱ፡፡

አባልነት

የማህበሩ መደበኛ አባል የሚሆነው፡-

– ድርጅቱ መደበኛ፣ የክብርና ተባባሪ እየተባሉ የሚጠሩ አባላት ይኖሩታል፡፡የአባልነት መብት ለወራሾችም ሆነ ለሌላ ሰው የማይተላለፍ የግል መብት ነው፡፡

– የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሃይማኖት ተከታይና የሰበካ ጉባዔ አባል የሆነ፣- የድርጅቱን ዓላማ የተቀበለ፣ በጠቅላላ ጉባዔው የተወሰነውን ወርሀዊና ዓመታዊ የአባልነት መዋጮ ለመክፈል    የተስማማ፣ማህበሩን በሙያ፣ በጉልበትም ሆነ በገንዘብ ለመርዳት ፈቃደኛ የሆነ፣ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ፣ከዚህ በላይ የተመለከቱትን መስፈርቶች አሟልቶ የማህበሩ አባል ለመሆን ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ያገኘ ሰው የማሕበሩ አባል ነዉ፡፡

What's new?